https://t.me/combankethofficial/9923?single
https://t.me/combankethofficial/9923?single
T.ME
Commercial Bank of Ethiopia - Official
“ሁሉም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ኑሮ የማሻሻል ግዴታ አለበት” አቶ አቤ ሳኖ ****************** ዛሬ በባንካችን ዋና መ/ቤት በተከበረው “አዲሱን ዓመት ከፕሬዝዳንታችን ጋር!” መርሃ ግብር ላይ የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደተናገሩት ሁሉም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ኑሮ የማሻሻል ግዴታ አለበት። ከ83 ዓመት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ መንግስታት አስፈላጊ ሆኖ በመቀጠል የባንክ አገልግሎትን በማላመድ እና በማዳረስ እንዲሁም የኢኮኖሚ ነጻነት ለመፍጠር በሚደረገው የዕድገት እንቅስቃሴ ላይ የማይተካ ሚና መጫወቱን አቶ አቤ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ያለፉ ትውልዶችን መልካም አርአያነት እና ስራ አክባሪነት በማስቀጠል ባንኩ የተጣለበትን ትልቅ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ማስቻል እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
0 Σχόλια 0 Μοιράστηκε 149 Views 0 Προεπισκόπηση