https://t.me/combankethofficial/9918?single
https://t.me/combankethofficial/9918?single
T.ME
Commercial Bank of Ethiopia - Official
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአምስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከ47.6 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ************** “አዲሱን ዓመት ከፕሬዝዳንታችን ጋር” በሚል መሪ ቃል በዋናው መሥሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ዛሬ በተከናወነው መርሀ ግብር ላይ ባንካችን ለአምስት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። መቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል፣ ባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፣ አበበች ጎበና የበጎ አድራጎት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ኩላሊት ህመም ማኅበር አጠቃላይ የ47.6 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። አቶ አቤ ባንካችን ከመደበኛ ሥራው በተጨማሪ በርካታ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የሚያስችሉ ሥራዎችን እንደሚሠራ በመርሐ ግብሩ ላይ ተናግረዋል። ባንካችን የዛሬውን ድጋፍ ጨምሮ ከ2017 በጀት ዓመት እስካሁን ከ917 ሚሊዮን ብር በላይ ለበጎ አድራጎት ሥራ አውሏል።
0 Kommentare 0 Geteilt 157 Ansichten 0 Bewertungen