በሩሲያ የተከሰተውን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ ጃፓን እና አሜሪካን እያስጨነቀ ነው
**************

በምስራቅ ሩሲያ በሬክተር ስኬል 8.8 የተመዘገበውን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ በማስከተል ጉዳት አድርሷል።

እጅግ ከባድ ነው የተባለለትን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ በጃፓን፣ በአሜሪካዋ ሃዋይ እና በሌሎች የአሜሪካ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻዎች አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ስጋት ደቅኗል።

በሩሲያ ካምቻትካ ባሕረ ሰላጤ የተከሰተው እና ከ3- እስከ 4 ሜትር ከፍታ ያለው የሱናሚ ማዕበል በሰሜን ጃፓን የምትገኘውን ሆካይዶ ከተማን መትቷል።

የአሜሪካዋ ሃዋይ አገረ ገዢ ጆሽ ግሪን፣ ነዋሪዎች ንቁ እንዲሆኑ እና ነገሩ ከከፋም አካበቢያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ አሜሪካውያን ለሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች ንቁ እንዲሆኑ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም በቻይና፣ በፊሊፒንስ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በጉዋም፣ በፔሩና በኢኳዶር በሚገኙ ጋላፓጎስ ደሴቶች ላይ የተለያዩ መጠን ያላቸው የሱናሚ አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተገልጿል።

ቢቢሲ በቅርብ ሰዓት ባጋራው መረጃ ማዕበሉ ሃዋይ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ እና ፈጣን እርምጃዎች መወሰድ እንዳለበትም እያመላከተ ነው ተብሏል፡፡

በለሚ ታደሰ

#sunami #earthquake #ebcdotstream
በሩሲያ የተከሰተውን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ ጃፓን እና አሜሪካን እያስጨነቀ ነው ************** በምስራቅ ሩሲያ በሬክተር ስኬል 8.8 የተመዘገበውን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ በማስከተል ጉዳት አድርሷል። እጅግ ከባድ ነው የተባለለትን ርዕደ መሬት ተከትሎ የተነሳው ሱናሚ በጃፓን፣ በአሜሪካዋ ሃዋይ እና በሌሎች የአሜሪካ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻዎች አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ስጋት ደቅኗል። በሩሲያ ካምቻትካ ባሕረ ሰላጤ የተከሰተው እና ከ3- እስከ 4 ሜትር ከፍታ ያለው የሱናሚ ማዕበል በሰሜን ጃፓን የምትገኘውን ሆካይዶ ከተማን መትቷል። የአሜሪካዋ ሃዋይ አገረ ገዢ ጆሽ ግሪን፣ ነዋሪዎች ንቁ እንዲሆኑ እና ነገሩ ከከፋም አካበቢያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ አሜሪካውያን ለሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች ንቁ እንዲሆኑ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በቻይና፣ በፊሊፒንስ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በጉዋም፣ በፔሩና በኢኳዶር በሚገኙ ጋላፓጎስ ደሴቶች ላይ የተለያዩ መጠን ያላቸው የሱናሚ አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተገልጿል። ቢቢሲ በቅርብ ሰዓት ባጋራው መረጃ ማዕበሉ ሃዋይ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ እና ፈጣን እርምጃዎች መወሰድ እንዳለበትም እያመላከተ ነው ተብሏል፡፡ በለሚ ታደሰ #sunami #earthquake #ebcdotstream
0 Comentários 0 Compartilhamentos 783 Visualizações 0 Anterior
Gojjochat https://gojjochat.com