ከመስከረም ጀምሮ የሚጠጣ ዉሐ ላታገኙ ትችላላችሁ ! / ቴህራን /
ኢራን በገጠማት የመጠጥ ዉሐ እጥረት ምክንያት ጭንቅ ላይ መሆኗ ተሰማ ።
ህዝቡ የውሃ ፍጆታን ካልቀነሰ አጠቃቀሙን ካላስተካከለ ቴህራንን እስከ መስከረም ወር ድረስ ለከባድ እጥረት ሊያጋጥማትና ለመጠጥም ሊቸግር እንደሚችል የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን ተናግረዋል ሲል የሀገሪቱ ኦፊሴላዊ የታስኒም የዜና ወኪል ሐሙስ ዘግቧል ።
ፔዝሽኪያን ሐሙስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በቴህራን ማስተዳደር ካልቻልን እና ሰዎች ፍጆታን ለመቆጣጠር ካልተባበሩ በመስከረም ወይም በጥቅምት ግድቦች ውስጥ ምንም ውሃ አይኖርም” ብለዋል ።
ከአሁን በፊት ሰኞ ዕለት በካቢኔው ባደረጉት ስብሰባ ላይ “የውሃ ቀውሱ ዛሬ ከሚነገረው የበለጠ አሳሳቢ ነው፣ እናም ዛሬ አስቸኳይ ውሳኔዎችን ካላደረግን ወደፊት ሊድን የማይችል ሁኔታ ይገጥመናል” በማለት ተናግረዉ የነበሩቴ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመሄዱ በዛሬው መግለጫ የጥንቃቄ መልዕክት ለዜጎች አስተላልፈዋል ።
የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተር ሼና አንሳሪ እና የሜትሮሎጂ ድርጅት የችግሩን አሳሳቢነትና ምክንያቱን የገለፀ ሲሆን ላለፉት አምስት አመታት ባጋጠማት ድርቅ ባለፉት አራት ወራት የዝናብ መጠን ከረጅም ጊዜ አማካይ ጋር ሲነጻጸር 40 በመቶ ቀንሷል ሲል ገልጿል ።
አክሎም "ዘላቂ ልማትን ችላ ማለታችን አሁን እንደ የውሃ ጭንቀት ያሉ በርካታ የአካባቢ ችግሮች እያጋጠሙን እንድንሆን አድርጎናል" ሲል አንሳሪ ሐሙስ ዕለት ለመንግስት ሚዲያ ተናግሯል።
የተትረፈረፈ የውሃ ፍጆታ በኢራን የውሃ አያያዝ ትልቅ ፈተናን የሚያመለክት ሲሆን የቴህራን ግዛት የውሃ እና ቆሻሻ ውሃ ኩባንያ ኃላፊ ሞህሰን አርዳካኒ ለመህር የዜና ወኪል እንደተናገሩት 70% የቴህራን ነዋሪዎች በቀን ከመደበኛው 130 ሊትር በላይ ይጠቀማሉ ሀገሪቱ ዙርያዋን በዉሐ የተከበበች ቢሆንም ጨዋማና ለምግብና መጠጥ አገልግሎት አይዉልም ሲል ያስነበበዉ ሮይተርስ ነዉ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

0 Commenti
0 condivisioni
288 Views
0 Anteprima