https://t.me/combankethofficial/9598
https://t.me/combankethofficial/9598
T.ME
Commercial Bank of Ethiopia - Official
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋላን ጨምሮ የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ህጋዊ ስርዓቱን ጠብቆ ወደ ሀገር የሚገባበትን መንገድ ማመቻቸት ላይ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ፡፡ =========================== ፕሬዚዳንቱ በዱባይ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የዲያስፖራ ቁጥር ቢኖራትም ከውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር እና ግኝት ጋር በተያያዘ ያለው አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደሆነ ገልጸዋል። ይሄን ለማሻሻል ባንካችን በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በተለይ አል-አንሳሪ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ከተባለ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋም ጋር በነበራቸው ውይይት ዱባይ እና አካባቢዋ በሚገኙ ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ የሚገኝ እንደመሆኑ ቀላል እና ተደራሽ የገንዘብ ማስተላለፊያ ማበልጸግ በሚቻልበት ሂደት ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል። የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ከአል-አንሳሪ ኤክስቼንጅ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ረሺድ አል አንሳሪ ጋር በነበራቸው ውይይት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ተወዳዳሪ የሆነ ዋጋ በማቅረብ የገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎት መስጠት ስለሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል። በተጨማሪም ለሁሉም በቀላሉ ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት በማስተዋወቅ ማህበረሰቡ ወደ ህጋዊ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት የሚመጣበትን ሁኔታ ማመቻቸት ላይ ተነጋግረዋል። በመጨረሻም ሁለቱም ተቋማት ህጋዊ የገንዘብ ማስተላለፍ ጋር በተያያዘ በጋራ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ለመስራት ተስማምተዋል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የሚመራው የልዑካን ቡድን ከተለያዩ…
0 Comments 0 Shares 183 Views 0 Reviews